ከ 20 ዓመታት በላይ ሚቺጋንን በማገልገል ላይ

 

 

ከ 20 ዓመታት በላይ ሚቺጋንን በማገልገል ላይ

 

 

ስለ

ስለቤተክርስቲያኒቱ

እ.ኤ.አ. በ1999 የተመሰረተችው የሚቸጋን ደብረመዊ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሜትሮ ዲትሮይት አካባቢ ማህበረሰብን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ እሴት እና ትውፊት ጋር በሚስማማ መልኩ ከ20 ዓመታት በላይ ስታገለግል ቅይታለች።

የእምነት አቋም

የእምነት አንቀጽ

ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ   በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደል የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም የሆነ የለም። በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለሰው ስለ መዳኛችን ከሰማይ ወረደ። ከመንፈስ ቅዱስ የተነሣ ከቅድስት ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሆኖ በጰንጤናዊበጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ። ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረም፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳትመጽሐፍት እንደ ተጻፈ።በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። ዳግመኛ ሕያዋንን ሙታንንም ይገዛ ዘንድበጌትነት ይመጣል። ለመንግሥስቱም ፍጻሜ የለውም። ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ፤ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ።ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንምእናምናለን።ኃጥያትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት አናምናለን።የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።”

የመንፈሳዊ ሕይወት ልምምድዎን ዛሬ ከእኛ ጋር ይጀምሩ!

አባል ይሁኑ